የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በተደረጉ አራት ጨዋታዎች ሲጠናቀቅ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸንፈዋል።
አራት ሰዓት ላይ ኤሌክትሪክን ከአዲሰ አበባ ከተማ ጋር ባገናኘው ጨዋታ በአዲስ አበባ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ የማሸነፊያ ግቢ በ35ኛው ደቂቃ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ በግንባር ገጭታ ሰብለ ቶጋ በማስቆጠር ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ኤሌክትሪኮች ወደፊት ገፍተው በመጨዎት ጫነ የፈጠሩ ሲሆን ብዙ ለግቢ የሚሆኑ ኳሶችን ሳይጠቀሙ ቀርተዋል እንዲሁም በ88ኛው ደቂቃ ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት ምርቃት ፈለቀ ብትመታም የአዲስ አበባዋ ግብ ጠባቂ በቀላሉ በመያዟ ለሽንፈት ተዳርገዋል።
በማስከተል 5:00 በተደረገው ጥሩ እንቅስቃሴ በታየው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ 3ለ1 በሆነ ግቢ ልዩነት ሲያሸንፍ ለሀዋሳ ከተማ የማሸነፊያ ግቦችን ፀሐይነሽ ጁላ፣እሙሽ ዳንኤል እና ቱሪስት ለማ ሲያስቆጥሩ በመጀመሪያ አጋማሽ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ የታየችዋ ፀሐይነሽ ጁላ ከፍፁም ቅጣት ምት መምቻ ውጪ አክርራ ቀመታችው ጎል 1ለ0 ለእረፍት ወጥተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽም ኳስን ተቆጣጥረው በፍፁም ጨዋታ በላይነት የተጫወቱት ሀዋሳ ከነማዎች በ51ኛው ደቂቃ እሙሽ ደንኤል ከመስመር የተሻገረላትን ኳስ በግንባር በመግጨት ወደ ግብነት በመቀየር መሪነታቸውን ማጠናቀር ሲትችል በተደጋጋሚ ወደተቃራኒ ግብ ክልል የበእርስ በእርስ ቅብብል ወደ ሳጥን ውስጥ በመግባት ቱረስት ለማ ባስቆጠረችው ግቢ መሪነታቸውን 3ለ0 ማድረግ ችለው ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከሽንፈት ያልተገቻቸውን ግብ ምስራቅ ዛቶ ባለቀ ደቂቃ 90+2 ላይ አስቆጥራለች።
ብዙም ሳቢ ባልነበረው የ8:00 ጨዋታ ወደ ግብ የሚደርሱ ኳሶች ብዙም አልታዩበትም። በዚህም መሰረት መቻልን ከሲዳማ ቡና ያገናኘው ጨዋታ 0ለ0 በሆነ ውጤት ሲጠናቀቅ መቻሎች በተደጋጋም ወደሲዳማ ቡና ግቢ ክልል ኳሶቹን ማድረስ ቢችሉም ጠንካራ ሆኖ የዋለው የሲዳማ ቡናው የተከላካይ መስመር ኳሶቹን በቀላሉ ከግን አከባቢ ሲያርቁ ተመልክተናል። ሲዳማ ቡና በአንፃሩ ረጃጅም ኳሶችን ሲጫወቱ የተመለከትን ሲሆን ከተከላካይ ጀርባ የሚጣሉ ኳሶችን ብዙም ሳይጠቀሙ በመቅረታቸው መጥብ መጋራት ችለዋል።
የሳምንቱ ማሰረጊያ በነበረው በ10:00 ሰዓቱ ጨዋታ ንግድ ባንክ ሀምበሪቾን የገጠመ ሲሆን ንግድ ባንክ የጨዋታ ብልጫ በመውሰድ ከአንደኛው ሳምንት ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሰዋል። በዚህም መሠረት ንግድ ባንክ 3ለ1 በሆነ ውጤት ሲየሸንፍ ሦስቱንም የማሸነፊያ ግቢ ሎዛ አበራ በ25ኛው ከሳጥም ውጪ በማስቆጠር ቡድኗን ቀዳሚ ማድረግ ችላላች። እንዲሁም ከባከነ ደቂቃ ውጪ ለእረፍት አምስት ያህል ደቂቃዎች ቀርተው እያለ በሰናፍ ዋቁማ ላይ በተሰራው ጥፋት ንግድ ባንኮች ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት ሎዛ አበራ በማስቆጠር 2ለ0 በሆነ ውጤት ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽም በደተጋጋሚ ወደ ሀንበሪቾ ግቢ ክልል ኳሶችን ይዛ እየገባች የጨዋተው ክስተት የነበረቺው ሎዛ አበራ በ70ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን አከባቢ ሆና አክርራ በመምታት 3 ለ0 እንዲመሩ አድርጋች። የሀምበሪቾን ብቸኛ ግቢ ሁለተኛ አጋማሽ እንደጀመረ በ46ኛው ደቂቃ ላይ ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ምት ብርሃን ኋይለስላሴ አስቆጥራ ጨዋታው 3ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ሊጉ ከሁለት ቀናት ዕረፍት በኋላ በመጪው ሰኞ በሦስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች እንደሚመለስ ይጠበቃል።