አስራት መገርሳ ከአልጄርያ ጋር የሚደረጉትን ጨዋታዎች በአምበልነት ይመራል

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ኢትዮጵያ ከ አልጄርያ ጋር ለምታደርጋቸው ተከታታይ ጨዋታዎች አማካዩ አስራት መገርሳን አምበል አድርገው መሾማቸውን አስታውቀዋል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ ወደ አልጄርያ ከማምራቱ በፊት በኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ አስራት መገርሳ ለሁለቱ ጨዋታዎች አምበል ተደርጎ መመረጡን ተናግረዋል፡፡ አስራት በአምበልነት ሹመቱ ደስታ እንደተሰማው ከሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡

“አምበል በመሆኔ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ ሀገርን የመምራት ፣ የቡድኑን መንፈስ አንድ የማድረግ እና ልምዴን የማካፈል ሀላፊነት ተጥሎብኛል፡፡ ይህንን ሀላፊነት ለመወጣትም ተዘጋጅቻለሁ ብሏል፡፡

የዳሽን ቢራው አማካይ በጉዳት ከብሄራዊ ቡድን ሮቆ በቅርቡ ከተመለሰ በኋላ በቻን 2016 መልካም እንቅስቃሴ ያሳየ ሲሆን በብሄራዊ ቡድኑ ስብስብ ልምድ ካካበቱ ተጫዋቾች መካከል ዋንኛው ሲሆን ከዚህ በፊት ዋልያዎቹን በአምበልነት መርቶ ባያውቅም በቀድሞ ክለቡ ኤሌክትሪክ አምበል እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *