የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ቀደም ብሎ ባሳወቀው የዝውውር ጊዜ ላይ ማስተካከያ መደረጉን አስታወቀ
የ2017 የውድድር ዘመን የዝውውር መስኮት ሐምሌ 15 እንደሚከፈት መግለፁ ይታወሳል፤ ፌደሬሽን አሁን ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ደግሞ የሚከፈትበት ቀን ላይ ማስተካከል ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ቀደም ብሎ ሐምሌ 8 ላይ ክፍት እንደሚሆን ገልጿል። ፌደሬሽኑ መስኮቱ የሚከፈትበት ዕለት ይፋ ቢያደርግም ከዚ ቀደም ጥቅምት መጀመርያ ላይ ያበቃል የተባለው የዝውውር ወቅት ላይ ግን ያለው ነገር የለም