በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊ ክለቦች መካከል እየተደረገ የሚገኘው የጥሎ ማለፍ ውድድር ዛሬ አንድ ጨዋታ አስተናግዶ የአምናው አሸናፊ መከላከያ ወላይታ ድቻን 3-0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው አልፏል፡፡
መከላከያ በመጀመርያው አጋመሽ የነበረውን የበላይነት ወደ ግብነት መቀየር የቻለው በ29ኛው ደቂቃ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት በበሃይሉ ግርማ አማካኝነት በማስቆጠር ነበር፡፡ ከእረፍት መልስ ወላይታ ድቻ ግብ ለማስቆጠር ሙሉ ለሙሉ ወደ ማጥቃቱ ሲያተኩር መከላከያዎች በመልሶ ማጥቃት የግብ እድሎችን ለመፍጠር ችለዋል፡፡ በ64ኛው ደቂቃ ላይ ሽመልስ ተገኝ ከቅጣት ምት ያሻገረውን ኳስ ባዬ ገዛኸኝ በግንባሬሩ በመግጨት የቀድሞ ክለቡ መረብ ላይ አሳርፏል፡፡ በ84ኛው ደቂቃ ላይ በጥሩ የመልሶ ማጥቃት የተገኘውን ኳስ ባዬ ገዛኸኝ ወደ ግብነት በመቀየር መከላከያ የ3-0 ድል እንዲያስመዘግብ አድርጓል፡፡
ድሉ መከላከያን ወደ ሩብ ፍጻሜው ያሻገረው ሲሆን በዚህ ወር መጨረሻ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ ከደደቢት ጋር ይፋለማል፡፡
የግማሽ ፍፃሜው ፕሮግራም የሚከተለውን ይመስላል፡-
መጋቢት 28 ቀን 2008
11፡30 መከላከያ ከ ደደቢት (አአ ስታድየም)
ሚያዝያ 2 ቀን 2008
09፡00 ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አአ ስታድየም)
11፡30 ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ (አአ ስታድየም)
-ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከተማ (ወደፈት ይገለፃል)