[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ከ15 ቀናት እረፍት በኋላ እንደሚጀመር ተገልፆ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ውድድር የሚጀመርበት ቀን ተራዝሟል፡፡
የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በአስራ ስድስት ክለቦች መካከል በሀዋሳ እንዲሁም ደግሞ በአሁኑ ሰዓት በድሬዳዋ ከተማ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያው ዙር የአስራ አምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሰሞኑ እየተደረጉ የሚገኝ ሲሆን ነገ ረቡዕ ሁለት ጨዋታ ከተደረጉ በኋላ ዙሩ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
በቀጣይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሁለተኛው ዙር ውድድር ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን አወዳዳሪው አካልም ከየካቲት 24 ጀምሮ ለአስራ አምስት ቀናት እረፍት እንደሚኖር ገልፆ ነበር። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችሁ መረጃ መሠረት ግን የእረፍት ቀኑ ወደ 27 ቀናት ተራዝሟል። በዚህም መጋቢት 19 አዳማ ላይ ሁለተኛው ዙር በይፋ የሚጀመር ይሆናል፡፡