ስዩም ተስፋዬ ከብሄራዊ ቡድን ውጪ ሲሆን አብዱልከሪም በምትኩ ተጠርቷል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በጉዳት መታመሱን ቀጥሎ ስዩም ተስፋዬ በጉዳት ከቡድኑ ውጪ የሆነ ሌላው ተጫዋች ሆኗል፡፡ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌም በኢትዮጵያ ቡና መልካም የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው አብዱልከሪም መሃመድን በስዩም ምትክ መርጠዋል፡፡

የብሄራዊ ቡድኑ አምበል ከትላንቱ ልምምድ በብሽሽት ጉዳት ምክንያት አቋርጦ የወጣ ሲሆን በዛሬው እለትም የቡድኑን ልምምድ ተቀምጦ ለመመልከት ተገዷል፡፡ የስዩም ጉዳት ከ3-4 ሳምንት እረፍት የሚያስፈልገው በመሆኑ ከአልጀርያ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ እንደማይደርስ በህክምና ተረጋግጧል፡፡ በስዩም ምትክ የብሄራዊ ቡድኑ ጥሪ የደረሰው አብዱልከሪም መሃመድ ዛሬ 8፡00 ላይ ከክለቡ ጋር ልምምዱን ካደረገ በኋላ ማታ ብሄራዊ ቡድኑ ወዳረፈበት ካፒታል ሆቴል በማምራት ቡድኑን የሚቀላቀል ሲሆን ነገ የመጀመርያ ልምምዱን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከ2015 ከማላዊ ብሄራዊ ቡድን ጋር ከተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ ለብሄራዊ ቡን ተሰልፎ የማያውቀው የቀኝ መስር ተከላካዩ አብዱልከሪም በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የስራ ዘመን መጀመርያ ለብሄራዊ ቡድ ከተጠሩ 44 ተጫዋቾች አንዱ የነበረ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት የመጨረሻው ዝርዝር ውስጥ ሳይካተት መቅረቱ የሚታወስ ነው፡፡ በብሄራዊ ቡድኑ ስዩም ተስፋዬ እና ታፈሰ ተስፋዬ በጉዳት ፣ ሳላዲን ሰሰኢድ ደግሞ ለጨዋታ ብቁ ባለመሆኑ ከአልጄርያው ጨዋ ውጪ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን በጉዳት የብሄራዊ ቡድን ልምምዱን እስካሁን ያልሰራው ሙሉአለም ጥላሁን ጉዳይም እስካሁን ቁርጡ አለየለትም፡፡

IMG_0128

የስዩም ተስፋዬ እና የሳላዲን ሰኢድ ከቡድኑ በውጪ መሆን አሰልጣን ዮሃነስ ሳህሌን አዲስ አምበል እንዲመርጡ ሲያስገድዳቸው በቻን ማጣርያ ከኬንያ ጋር በተደረገው ጨዋታ ቡድን በአምበልነት የመራው በሃይሉ አሰፋ አምበል የመሆን ቅድመ ግምት አግኝቷል፡፡ በዮሃንስ ሳህሌ እምነት ከሚጣልባቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ጋቶች ፓኖም እና ከፍተኛ የብሄራዊ ቡድን ልምድ ያላቸው አስራት መገርሳ እና ጌታነህ ከበደም በአምበልነት ሊሾሙ ይችላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *