የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ክሪስቲያን ጉርኩፍ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በተከታታይ ከአትዮጵያ ጋር ለሚያደጓቸው ጨዋታዎች የ23 ተጫዋቾችን ስም ይፋ አድርገዋል፡፡ ዴዘርት ዋርየርስ በሚል ተቀፅላ ስም የሚታወቁት አልጄርያዎች ከ2 ጨዋታ 6 ነጥብ በማግኘት ምድብ 10ን እየመራች የምትገኝ ሲሆን አርብ መጋቢት 16 ቢልዳ ከተማ ላይ ፣ ማክሰኞ መጋቢት 20 አዲስ አበባ ላይ በተከታታይ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ጨዋዋን ታደርጋለች፡፡
አሰልጣኝ ክሪስቲያን ጉርኩፍ በስብስባቸው ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከመረጧቸው መካከል የአንድ ተጫዋች ለውጥ በማድረግ የተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች ክለብ የሆነው ባንያስ ተጫዋች ኤሻክ ቤልፎዲልን በማስወጣት የሊሉ አጥቂ ያሲን ቤንዝያን በቡድናቸው አካተዋል፡፡ ፈረንሳይ የተወለደው የቀድሞው የሊዮን ተጫዋች ቤንዝያ ለአልጄርያ ለመጫወት የወሰነው በጥር ወር ነበር፡፡ በስብስቡ ከተካተቱት መካከል የፕሪሚየር ሊጉ ክስተት ሪያድ ማህሬዝ ፣ የስፖርቲን ሊዝበኑ ኢስላም ሲሊማኒ ፣ በናፖሊ መልካም የውድድር አመት እያሳለፈ የሚገኘው የግራ መስመር ተከላካዩ ፋውዚ ጉልሃም እንዲሁም በፖርቶ የተቀዛቀዘ የውድድር ዘን እያሳለፈ የሚገኘው ያቺን ብራሂሚ ይጠቀሳሉ፡፡
የ23 ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው፡-
ግብ ጠባቂዎች
አዛዲን ዶውካ (ጂኤስ ካቤሌ/አልጄርያ)
ሬይስ ሞቦሆሊ (አንታሊያስፖር/ቱርክ)
ማሊክ አሴላህ (ቤሎውዚዳድ/አልጄርያ)
ተከላካዮች
ሂቸም ቤልካሮይ (ናሲዮናል ማዴይራ/ፖርቱጋል)
ራሚ ቤንሴቤያኒ (ሞንፔሌ/ፈረንሳይ)
ነስረዲን ክሆውሌድ (ዩኤስኤም አልጀር/አልጄርያ)
ኤሳ ማንዲ (ስታድ ሬም/ፈረንሳይ)
ካርል ሜጃኒ (ሌቫንቴ/ስፔን)
መህዲ ዜፋን (ሬንስ/ፈረንሳይ)
ሞሃመድ ኮህቲር ዚቲ (ጂአኤስ ካቤሌ/አልጄርያ)
ፋውዚ ጉልሃም (ናፖሊ/ጣልያን)
ሜህዲ አቢዬድ (ፖናቲንያኮስ/ግሪክ)
ነቢል ቤንታሌብ (ቶተንሃም/እንግሊዝ)
ሪያድ ቦዴቦውዝ (ሞንፔሌ/ፈረንሳይ)
ያሲን ብራሂሚ (ፖርቶ/ፖርቱጋል)
ሶፊያን ፌጉይሊ (ቫሌንሺያ/ስፔን)
ዋሊድ መስሎብ (ሎርዮ/ፈረንሳይ)
ሰፊር ታይደር (ቦሎኛ/ጣልያን)
አጥቂዎች
ያሲን ቤንዚያ (ሊል/ፈረንሳይ)
ራሺድ ጌዛል (ሊዮን/ፈረንሳይ)
ሪያድ ማሃሬዝ (ሌይስተር ሲቲ/እንግሊዝ)
ኢስላም ስሊማኒ (ስፖርቲንግ ሊዝበን/ፖርቱጋል)
ሂላል ኤልአረብ ሱዳኒ (ዲናሞ ዛግሬብ/ክሮሺያ)
ፎቶ – ዲዜድ ፉት