[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የረጅም ዓመት ቆይታ ያደረገው ጋናዊው አማካይ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።
በአሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ የሚመራው አዲስ አበባ ከተማ ለሁለተኛው ዙር ውድድር ራሱን ለማጠናከር ቡድኑ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡት ከማይገኙ ተጫዋቾች ጋር በስምምነት እየተለያየ ይገኛል። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሰረትም ከነዚህ መካከል አንዱ የሆነው ጋናዊው የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች ጋብሬል አህመድ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።
በኢትዮጵያ እግርኳስ ከ2003 ጀምሮ በደደቢት፣ ንግድ ባንክ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ መቐለ እና ፋሲል ክለቦች ሲጫወት የቆየው አማካዩ በክረምቱ የዝውውር መስኮት አዲስ አዳጊውን ቡድን ቢቀላቀልም እምብዛም ግልጋሎት ሲሰጥ አልታየም።
በሌላ ዜና አዲስ አበባ ከተማዎች ጥቂት ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ እና በቅርቡ ዝውውሩን ይፋ እንደሚያደርጉ ሰምተናል።