[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በአሰልጣኝ ዘማርያም እና በድሬዳዋ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ሲከታተል የቆየው የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ አሳልፏል።
ድሬደዋ ከተማ አሰልጣኝ ዘማርያምን የሚፈለገውን ውጤት አላስገኙም በማለት በዕግድ አቆይቷቸው እንደነበር እና በኋላ ላይ ደግሞ ጥሪ በማስተላለፍ ከ20 ዓመት በታች ቡድኑን ዝቅ ብለው እንዲያሰለጥኑ ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ይህን ውሳኔ በመቃወም አሰልጣኝ ዘማርያም ለፌዴሬሽኑ ዲሲፒሊን ኮሚቴ ቅሬታቸውን አቅርበው እየተከታተሉ በሉበት ወቅት ክለቡ በትናንትናው ዕለት አሰልጣኙን በማሰናበት አዲስ አሰልጣኝ መሾመን ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል የፌዴሬሽኑ የዲሲፒሊን ኮሚቴ የሁለቱን ወገኖች አቤቱታ ከመረመረ በኋላ ውሳኔ ሰጥቷል። በውሳኔውም መሠረት አሰልጣኝ ዘማርያምን ወደ ተቀጠሩበት ፕሪምየር ሊግ ውድድር አሰልጣኝነት እንዲመለሱ ክለቡ ይህን ካልፈለገ ግን በውላቸው መሠረት ተፈፃሚ እንዲያደርግ እና ያልተከፈለውን ደመወዝ ለአሰልጣኙ እንዲከፍል ተወስኗል። ክለቡ ይህ ውሳኔ በደረሰው በሰባት ቀናት ውስጥ ውሳኔውን ተፈፃሚ እንዲያደርግ ፌዴሬሽኑ ያዘዘ ስሆን ውሳኔውን ተፈፃሚ የማያደርግ ከሆነ ከፌዴሬሽኑ ምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳያገኝ እና ከፕሪምየር ሊጉ ውድድር እንዲታገድ ተወስኗል። ድሬዳዋ ከተማ በውሳኔው ላይ ይግባኝ መጠየቅ መብት እንዳለውም ተጠቅሷል።