[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው መከላከያ ከደቂቃዎች በፊት የተከላካይ መስመር ተጫዋች አስፈርሟል።
በዘንድሮ የውድድር ዓመት ከሁለተኛው የሊግ እርከን ወደ ዋናው ፕሪምየር ሊግ ያደገው መከላከያ የመጀመሪያውን ዙር ውድድር በ18 ነጥቦች 11ኛ ደረጃን በመያዝ እንዳገባደደ ይታወቃል። ባሳለፍነው ሳምንት በተከፈተው የሁለተኛ ዙር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በስፋት እንደሚሳተፍ የተገለፀው ክለቡም ከደቂቃዎች በፊት የተከላላይ መስመር ተጫዋቹ አሚኑ ነስሩን የግሉ አድርጓል።
የቀድሞ የጅማ አባ ጅፋር እና መቐለ 70 እንደርታ ተጫዋች የነበረው አሚኑ ከአዳማ ከተማ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ የዝውውር መስኮቱ እስኪከፈት ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲደራደር የቆየ ሲሆን አሁን በ16 ወራት ኮንትራት ማረፊያውን ጦሩ ቤት አድርጓል። በተከታታይ (2010 እና 2011) የሊጉን ዋንጫ ያገኘው ተጫዋቹ ከአሌክስ ተሰማ እና ኢብራሒም ሁሴን ጋር ቀዳሚ ቦታን ለማግኘት የሚያደርገው ፉክክር ይጠበቃል።