[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ባለፉት ዓመታት ለወልቂጤ ከተማ ግልጋሎት ሲሰጥ የቆየው አጥቂ ዛሬ ከክለቡ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ መዳረሻው አዞዎቹ ቤት ሆኗል።
አሰልጣኝ ተመስገና ዳና በሚፈልጉት መንገድ ቡድኑን ለማጠናከር በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ሲታወቅ የተፈለገውን ያህል አገልግሎት አልሰጡም ተብሎ ከሚታመኑ ተጫዋቾች ጋር በስምምነት መለያየት ጀምረዋል። አህመድ ሁሴንም ከክለቡ ጋር የተለያየ ተጫዋች ሆኗል።
የቀድሞው የቡታጅራ ከተማ አጥቂ ወደ ሠራተኞቹ ካመራ በኋላ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደረገ ሲሆን ቀሪ የስድስት ወር ኮንትራት ቢኖረውም ከወልቂጤ ከተማ ጋር ዛሬ በስምምነት ተለያይቷል። ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር ከተለያየ በኋላም ወደ አርባምንጭ ከተማ ጉዞውን አድርጓል። አህመድ ለአንድ ዓመት የሚያቆየውን ፊርማ በፌዴሬሽን በመገኘት ማኖሩንም ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋች እንደሚያስፈርሙ የሚጠበቁት አርባምንጮች ከተለያዩ ተጫዋቾቻቸው ጋር በስምምነት ይለያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰምተናል።