[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ወልቂጤ ከተማ በመስመር እና በአማካይ ክፍል ላይ ሊጠቀምበት የሚችለውን ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን በመጀመሪያው ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻዎቹ ሦስት ቀሪ ጨዋታዎች ሲቀሩ የቀጠረው ወልቂጤ ከተማ ለሁለተኛው ዙር ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ ይረዳው ዘንድ ከቀናት በፊት ከዩጋንዳዊው ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ ጋር የተስማማ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ በአንድ ዓመት ውል ቤዛ መድህንን ቀዳሚ የፋዊ ፈራሚው ማድረጉን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡
በመስመር አጥቂነት እና በአማካይ ስፍራ ተጫዋቾችነት የሚጫወተው ቤዛ ከመከላከያ ተስፋ ቡድን የተገኘው ሲሆን በሀድያ ሌሙ ክለብ በ2011ቆይታ በማድረግ የአንደኛ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አጠናቆ ነበር። ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢኮስኮ ዘንድሮ ደግሞ የ2014 የከፍተኛ ሊግ ውድድር በምድብ ሀ በሚገኘው ገላን ከተማ የመጀመሪያውን ዙር ሙሉ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፏል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ በሁለት ጨዋታዎች ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያሳለፈው ቤዛ በዚህ ዓመት ሦስተኛ ክለቡ የሆነው ወልቂጤ ከተማን በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን በዛሬው ዕለት በመገኘት በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሏል።
ተጫዋቹ ከዓመታት በፊት በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና በሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ አባል በመሆን ከአሁኑ አሰልጣኙ ጋር ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል፡፡