ደደቢት ከሱር ኮንስትራክሽን የአውቶብስ ስጦታ ተበረከተለት

የደደቢት እግርኳስ ክለብ ዛሬ በጦር ሃይሎች መኮንኖች ክበብ ከሱር ኮንስትራክሽን የተበረከተለትን የተጫዋቾች ማጓጓዣ አውቶብስ አስተዋውቋል፡፡

ከሱር ኮንስትራክሽን የተበረከተው አውቶብስ 45 ሰዎችን መያዝ የሚችል ሲሆን 2.3 ሚልዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡ በአውቶብሱ ላይም የሱር ኮንስትራክሽን አርማ በጉልህ ተደርጓል፡፡

በርክክብ ስነስርአቱ ላይ ሱር ኮንስትራክሽንን በመወከል አቶ ታደሰ የተገኙ ሲሆን ባደረጉት ንግግርም ደደቢት ወደ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ክለብነት ለመሸጋገር የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ይህ የአውቶብስ ስጦታ አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ አመታትም ከክለቡ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልፃዋል፡፡

በደደቢት በኩል የቴክኒክ ዳይሬክተሩ አቶ ሚካኤል አምደመስቀል ከሱር ኮንስትራክሽን ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ከኩባንያው ጋር ያላቸው ግንኙነት በቀጣይ አመት ወደ አጋርነት እንደሚሸጋገር ገልፀዋል፡፡ ከሱር ጋር በአሁኑ ሰአት ያላቸው ግንኙነት ከክለቡ ባሻገር ድርጅቱን ተጠቃሚ እንደማያደርግ አምነው ለሱር እንደ ትልቅ ስኬት የሚታየው ማህበራዊ ሃላፊነቱን መወጣቱ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

በርክክብ ፕሮግራሙ የወንዶቹ ቡድን አምበል ብርሃኑ ቦጋለ እና የሴቶቹ ቡድን አምበል ኤደን ሽፈራው ተጫዋቾችን በመወከል ሱር ኮንስትራክሽንን አመስግነዋል፡፡

በፕሮግራሙ መጨረሻ የክለቡ እና የሱር ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ፣ የወንድ እና ሴቶች ቡድን አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች በጋራ በመሆን የፎቶ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡

PicsArt_1459594902378 PicsArt_1459595042989 PicsArt_1459594817898

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *