ለ2017 ከ20 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ነገ ሶማልያን የሚያስተናግደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን በቀትር በኋላ አከናውኗል፡፡
ጥቂት ደቂቃዎች በፈጀው የልምምድ ፕሮግራም ቡድኑ ተጫዋቾቹን 5 ቦታ በመከፋፈል ቀላል የማላቀቅያ ልምምዶችን አከናውኗል፡፡
ለነገው ጨዋታ 25 ተጫዋቾች ብቁ የሆኑ ሲሆን አማካዩ ዘሪሁን ብርሃኑ በፓስፖርት ጉዳዮች ምክንያት የነገው ጨዋታ እንደሚያልፈው ታውቋል፡፡
ግብ ጠባቂዎች
ተክለማርያም ሻንቆ – አዲስ አበባ
ክብረአብ ዳዊት – ሀዋሳ ከተማ
በሽር ደሊል – ሙገር ሲሚንቶ
ምንተስኖት የግሌ – ደደቢት
ተከላካዮች
ዳግም ንጉሴ – ወላይታ ድቻ
ፈቱዲን ጀማል – ወላይታ ድቻ
ተስፋዬ ሽብሩ – አዲስ አበባ ፖሊስ
ሙጀኢድ መሃመድ – መከላከያ
ሀይደር ሙስጠፋ – ጅማ አባ ቡና
እንየው ካሳሁን – አዲስ አበባ ከተማ
ደስታ ደሙ – ሙገር ሲሚንቶ
ያሲን ጀማል – አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ዳንኤል ራህመቶ – አዲስ አበባ ፖሊስ
አማካይ
መርዋን ራያ – ሙገር ሲሚንቶ
እያሱ ታምሩ – ኢትዮጵያ ቡና
ከንአን ማርክነህ – አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ኤፍሬም ካሳ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሱራፌል ዳኛቸው – አዳማ ከተማ
ኡጁሉ ኦክሎ – ጋምቤላ ከተማ
ዳዊት ተፈራ – ጅማ አባቡና
ክንዳለም ፍቃዱ – ሙገር ሲሚንቶ
በሱፍቃድ ነጋሽ – መቀለ ከተማ
አጥቂዎች
ያሬድ ብርሀኑ – ደደቢት
ኦሜ መሃመድ – ጅማ አባ ቡና
ሱራፌል አወል – ጅማ አባቡና