ኢትዮጵያ 2-1 ሶማልያ
ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከሶከር ኢትዮጵያ
– – – – – –
ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በኢትዮጵያ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ቢጫ ካርድ
88′ ተስፋዬ ሽብሩ ኳስ ሲሻማ የሶማልያ ተጫዋች በመማታቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
85′ ኤፍሬም ካሳ ገብቶ እያሱ ታምሩ ወጥቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
80′ ሀሰን ሲዶ ግቧ ከመስመር አላለፈችም ብሎ ከዳኛ ጋር ውዝግብ ውስጥ በመግባቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመዞበታል፡፡
ጎልልል!!! ኢትዮጵያ
79′ ተስፋዬ ሽብሩ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ወደ ግብ ሲሞክር የሶማልያው ሳዳም ነክቶት ወደ ግብነት ተቀይሯል፡፡
ጎልልል!!!! ሶማልያ
77′ ኢሴ ኢብራሂም ከማዕዘን የተመታውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ሶማልያን አቻ አድርጓል፡፡
75′ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ ፈቱዲን በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
68′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
ከነአን ማርክነህ ገብቶ በሱፍቃድ ነጋሽ ወጥቷል፡፡
65′ ኦሜ መሃመድ ከርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ሶማልያ
አብድራሂም ኦስማን ወጥቶ አብድቃድር ሙህዲን ገብቷል
64′ ዳዊት ያሻገረውን ኳስ ክንዳለም ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
56′ በሱፍቃድ የመታውን ቅጣት ምት ግብ ጠባቂው ሙስጣፋ በቀላሉ ይዞበታል፡፡
54′ አብዲአዚዝ ሀቶሽ ከመስመር ወደ ውስጥ በማጥበብ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
52′ ክንዳለም ፍቃዱ ገብቶ ሱራፌለ ልዳኛቸው ወጥቷል፡፡
46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ
——-
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በኢትዮጵያ መሪነት ተጠናቋል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
40′ ዳንኤል ራህመቶ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሙስጣፋ ሁሴን ይዞበታል፡፡
39′ ኦሜ መሃመድ አንድ ተከላካይ በማለፍ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
34′ ፈይሰል ሀሺ ከተከላካዮች አምልጦ በመውጣት የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
ቢጫ ካርድ
29′ ኑር አሊ በዳዊት ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
26′ ጎልልል!!!
ሱራፌል አወል ከኦሜ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ኢትዮጵያን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
23′ ዳዊት ተፈራ ከቅጣት ምት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
15′ ኢትዮጵያ በኳስ ቁጥጥር የተሻለች ብትሆንም ጨዋታው ተመጣጣኝ እና ቀዝቀዘ ዝያለ እንቅስቃሴ እየታየበት ነው፡፡
ቢጫ ካርድ
6′ ኑኔ አህመድ ሱራፌል አወል ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው በኢትዮጵያ አማካኝነት ተጀመረ
– – – –
የኢትዮጵያ አሰላለፍ
ተክለማርያም ሻንቆ
እንየው ካሳሁን – ፈቱዲን ጀማል – ዳንኤል ራህመቶ – ተስፋዬ ሽብሩ
እያሱ ታምሩ – ሱራፌል ዳኛቸው – በሱፍቃድ ነጋሽ – ዳዊት ተፈራ
ኦሜ መሃመድ – ሱራፌል አወል
—-
የሶማልያ አሰላለፍ
ሙስጣፋ ሁሴን
ኑር አሊ – ሀሰን ሲዶው – ኢሴ ኢብራሂም – ሳዳም ጋብ
ኢብራሂም መሃመድ – ኑኔ አህመድ – አብዱልከሪም አብደላ – አብድላዚዝ አቶሽ
ፈይሰል ሀሺ – አብዱራሂም መሀመድ