መከላከያ 1-0 ደደቢት
88′ ባዬ ገዛኸኝ
ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከሶከር ኢትዮጵያ
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በመከላከያ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ጦሩ ለተከታታይ 4ኛ አመት ለሊጉ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ መድረሱን አረጋግጧል፡፡
90+2′ ባዬ ገዛኸኝ ቅጣት ምት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
88′ ጎልልል!!! መከላከያ
ባዬ ገዛኸኝ የጨዋታውን እጅግ ወሳኝ ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
80′ ዳዊት ፍቃዱ ወጥቶ ጆሴፍ አግዮኪ ገብቷል
75′ ጨዋታው እጅግ አሰልቺ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ነው፡፡ በቡድንም ሆነ በግል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የሌሉበትና የማሸነፍ ፍላጎት የማይታይበት ጨዋታ ሆኗል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
70′ ማራኪ ወርቁ ገብቶ ካርሎስ ዳምጠው ወጥቷል፡፡
67′ ሳሚ ሳኑሚ ያሻገረለትን ግልፅ የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ ዳዊት በማይታመን ሁኔተ ታአምክኖታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
62′ ሳሙኤል ሳሊሶ ወጥቶ ሳሙኤል ታዬ ገብቷል
57′ ባዬ ገዛኸኝ በተከላካዮች መሃል በማምለጥ የሞከረውን ኳስ ጆን ቱፎር ፣ ታሪክ ጌትነት እና የግቡ አግዳሚ ተጋግዘው አውጥተውበታል፡፡
ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡
የእረፍት ሰአት ቅያሪ – ደደቢት
ሄኖክ ኢሳያስ ገብቶ ኤፍሬም ጌታቸው ወጥቷል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
44′ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ ነጂብ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
28′ ባዬ ገዛኸኝ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል የግራ ጠርዝ አክርሮ የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
25′ ጨዋታው ቀዝቀዛ እና ብዙም ትኩረት የማይስብ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ነው፡፡
20′ ሳምሶን ጥላሁን ከቅጣት ምት የሞከረውን ኳስ ጀማል ጣሰው በቀላሉ ተቆጣጥሮታል፡፡
15′ ባዬ ገዛከኝ ከርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
14′ ዳዊት ፍቃዱ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ክልል በመግባት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
11′ ባዬ ገዛኸኝ በፈጣን ቅብብል ያገኘውን ኳስ ሞክሮ ታሪክ አድኖበታል፡፡
4′ ከታፈሰ ሰርካ ለፍሬው በረጅሙ የተላከውን ኳስ ታሪክ ጌትነት የግብ ክልሉን ለቆ በመውጣት አድኖታል፡፡
ተጀመረ
ጨዋታው በደደቢት አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
11:33 ቡድኖቹ ወደ ሜዳ በመግባት ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ፡፡
11:25 ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
11:10 ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተው በማማሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የደደቢት አሰላለፍ
ታሪክ ጌትነት
ስዩም ተስፋዬ – ጆን ቱፈር – ምኞት ደበበ – ተካልኝ ደጀኔ
ሽመክት ጉግሳ – ሄኖክ ካሳሁን – ሳምሶን ጥላሁን – ኤፍሬም ጌታቸው
ዳዊት ፍቃዱ – ሳሙኤል ሳኑሚ
ተጠባባቂዎች
ብርሃኑ ፍስሃዬ ፣ ብሩክ ተሾመ ፣ ወግደረስ ታዬ ፣ ሚኪያስ ፍቅሬ ፣ ሄኖክ ኢሳያስ ፣ ክዌሲ ኬሊ ፣ ጆሴፍ አማዮኬ
የመከላከያ አሰላለፍ
ጀማል ጣሰው
ታፈሰ ሰርካ – አዲሱ ተስፋዬ – ቴዎድሮስ በቀለ – ነጂብ ሳኒ
ሚካኤል ደስታ – በሃይሉ ግርማ – ፍሬው ሰለሞን – ሳሙኤል ሳሊሶ
ካርሎስ ዳምጠው – ባዬ ገዛኸኝ
ተጠባባቂዎች
ይድነቃቸው ኪዳኔ – ሚልዮን በየነ – ሙሉቀን ደሳለኝ – ቴዎድሮስ ታፈሰ – ማራኪ ወርቁ – ኡጉታ ኦዶክ – ሳሙኤል ታዬ
ማስታወሻ – የዚህ ውድድር ይፋዊ ስያሜ “የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር ” የሚል ነው፡፡ በሶከር ኢትዮጵያ ዘገባዎች ላይ “የሊግ ዋንጫ” በሚል ስያሜ የምንጠቀመው ለአጠራር እና አዘጋገብ አመቺ እንዲሆን በሚል ነው፡፡