የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ አስተናግዶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዳሽን ቢራን 2-1 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ከደደቢት ተረክቧል፡፡
ግብ በማስቆጠሩ ረገድ ቀዳሚ የሆኑት ዳሽን ቢራዎች ሲሆኑ በ6ኛው ደቂቃ ከመልሶ ማጥቃት የተገኘውን ኳስ የተሻ ግዛው በግሩም ሁኔታ አስቆጥሮ የጎንደሩን ክለብ ቀዳሚ አድርጓል፡፡
ከግቡ መቆጠር በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ጫና ፈጥረው ቢንቀሳቀሱም በተደራጀ ሁኔታ ሲከላከሉ የነበሩት የዳሽን ተከላካዮችን ሰብረው ግብ ማስቆጠር አልቻሉም፡፡ የመጀመርያው አጋማሽ የተጠናቀቀውም በዳሽን 1-0 መሪነት ነበር፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረው የተጫወቱት ፈረሰኞቹ የፈጠሩት ጫና ውጤት አስገኝቶ በ59 እና 61ኛው ደቂቃ በአዳነ ግርማ እና ምንተስኖት አዳነ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው መሪነቱን ቀልብሰውታል፡፡
ድሉ ቅዱስ ጊዮርጊስን በ26 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ ሲያስቀምጠው በመጪው ሰኞ በሌላ ተስተካካይ ጨዋታ መከላከያን ካሸነፈ ከተከታዩ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 4 አሳድጎ የመጀመርያውን ዙር ያጠናቅቃል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ