በዋልያዎቹ ምድብ የምትገኘው እና የቻን ውድድር አዘጋጅ የሆነችው አልጄሪያ የመጨረሻ ስብስቧን አሳውቃለች።
የዘንድሮ የቻን ውድድር አስተናጋጅ የሆነችው አልጄሪያ ለውድድሩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከሜዳ ውጪ በመስተንግዶ ሜዳ ላይ ደግሞ ቡድኗ ላይ የተለያዩ ሥራዎችን እየከወነች ትገኛለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሚገኝበት ምድብ 1 የተደለደለችው አልጄሪያ ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ የተለያዩ ተጫዋቾችን በመምረጥ ሀገሯ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ላይ ዝግጅቷን ስታደርግ ቆይታ የመጨረሻ ስብስቧን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጋለች።
በዚህም የቀድሞ የብሔራዊ ቡድኑ አምበል የነበሩት እና አሁን የቻን ቡድኑን እያሰለጠኑ የሚገኙት ማጂድ ቡግሄራ ሦስት የግብ ዘቦች፣ አስር ተከላካዮች፣ ሰባት አማካዮች እና ስምንት አጥቂዎችን በአጠቃላይ 28 ተጫዋቾችን በውድድሩ ለመጠቀም መርጠዋል።
ለዚህ ውድድር ዝግጅት በተለያዩ ቀናት እስካሁን አምስት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ያደረገው የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ ታኅሣሥ 29 ከጋና አቻው ጋር የመጨረሻ እንደሆነ የተገለፀውን የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ቀጠሮ እንደያዘ ማስነበባችን ይታወሳል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ስም ከሥር በምስሉ ተያይዟል 👇