ቻን | \”የአልጄሪያውን ጨዋታ እንደ ፍፃሜ ፍልሚያ እንቀርባለን\” ጋቶች ፓኖም

በትናንቱ የኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ጨዋታ ኮከብ ተብሎ የተመረጠው ጋቶች ፓኖም ምን አለ?

ኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ያደረጉት የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮንሺፕ የምድብ አንድ የመጀመሪያ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ መጠናቀቁ ይታወቃል። በዚህ ጨዋታ ላይ በዋልያው በኩል ከኳስ ጋር እና ከኳስ ውጪ ድንቅ ብቃት ሲያሳይ የነበረው የተከላካይ አማካዩ ጋቶች ፓኖም በውድድሩ አዘጋጅ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጧል። ተጫዋቹም ሽልማቱን ከተረከበ በኋላ ስለጨዋታው ያለውን ምልከታ እንደሚከተለው ተናግሯል።

\"\"

\”ስህተቶቻችንን ማረም ይገባናል ፤ አሁን የምንገኘው ትልቅ የውድድር መድረክ ላይ ነው። የተጋጣሚ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ስንገባ ውሳኔ ለመወሰን የምናመነታ መሆን አይገባንም። ቀጣይ ተጋጣሚዎቻችን የሆኑትን የአልጄሪያ እና የሊቢያን ጨዋታ ተመልክተናል። ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ የምንፈልግ ከሆነ ከእነሱ ጋር ስንጫወት የተሻለ ነገር ማድረግ ይጠበቅብናል።\”

\"\"

በመጨረሻም ስለቀጣዩ የአልጄሪያ ጨዋታ ጥያቄ የቀረበለት ጋቶች \”የአልጄሪያውን ጨዋታ እንደ ፍፃሜ ፍልሚያ እንቀርባለን። ስህተት ምንም ቦታ የለውም። በእግርኳስ ምንም ሊፈጠር ይችላል። እንሸነፋለን ብለን ወደ ግጥሚያው ከገባን ሻንጣዎቻችንን አዘጋጅተን ወደ ቤታችን ልንሄድ እንችላለን። ይሄ በጭራሽ ዐምሯችን ውስጥ የለም። እዚህ የመጣነው ለመፎካከር ነው።\” በማለት ሀሳቡን አገባዷል።