የሊጉ አክሲዮን ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ ምርጫውን ሊያካሂድ ነው

ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበርን የሚመሩ የቦርድ አመራሮች ምርጫ በዚህ ሳምንት ይደረጋል።

\"\"

የኢትዮጵያ ኘሪምየር ሊግ ክለቦች በራሳቸው አቅም ውድድሮቻቸውን ማስኬድ እንዲችሉ ሰባት አባላት ያሉት የውድድር አመራር አብይ ኮሚቴ በ2012 መምረጣቸው ይታወሳል። ኮሚቴው ከዓመት በኋላ ራሱን በማደራጀት ከዐብይ ኮሚቴ ወደ ሊግ አክሲዮን ማህበር በመቀየር የሊጉን ደረጃ ከፍ ያደረጉ በርከት ያሉ ሥራዎች እየከወነ ቆይቷል። አሁን ደግሞ በተቀመጠው ደንብ መሠረት በሦስት ዓመት አንዴ የሥራ አመራር ቦርድ ምርጫ የሚያካሄድ መሆኑን ተከትሎ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሊግ አክሲዮን ማህበር በሥራ አመራር ቦርድ የሚመሩ ሰባት አባላትን የሚለይ ምርጫ ያካሄዳል።

በዚህም መሠረት የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 16 ከረፋድ ጀምሮ በካፒታል ሆቴል የአስራ ስድስቱም ክለቦች ተወካዮች በተገኙበት ምርጫው እንደሚያካሂድ ታውቋል።

\"\"