ኢትዮጵያዊው ኢንስትራክተር ወደ አቡጃ ያመራሉ

የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ለናይጄሪያዊያን ባለሙያዎች የኢንስትራክተርነት ኮርስን ለመስጠት ዛሬ ወደ ስፍራው ያቀናሉ።

\"\"

ኢትዮጵያ ካሏት የእግርኳስ ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር እና የፊፋ ኤክስፐርት አብርሀም መብራቱ በዛሬው ዕለት ወደ ናይጄሪያ አቡጃ እንደሚያመሩ በተለይ ሶከር ኢትዮጵያ ለማወቅ ችላለች። ኢትዮጵያዊው ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ከሰሞኑ በሀዋሳ ከተማ ሲሰጥ የነበረውን የካፍ ሲ ላይሰንስ ስልጠናን ሲሰጡ የሰነበቱ ሲሆን በትላንትናው ዕለትም ይህን የላይሰንስ ስልጠና አጠናቀው ለሌላ ከፍ ያለ አህጉራዊ ስልጠና ደግሞ ለናይጄሪያዊያን ከፍተኛ ኢንትስትራክተሮች ኮርሶችን ለአስር ቀናት ያህል ለመስጠት በካፍ መመረጣቸውን ተከትሎ ነው ኢንስትራክተሩ ወደ ስፍራው እንደሚያመሩ ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።

\"\"

የካፍ ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ያለፉትን አስራ ስድስት ወራት ወደ አልጄሪያ ፣ ሲሼልስ ፣ ኬኒያ ፣ ላይቬሪያ እና ማላዊ ተጉዘው የኢንስትራክተርነት ኮርስን እና የአሰልጣኞች የላይሰንስ ስልጠናን መስጠታቸው ይታወሳል።