ወላይታ ድቻ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

የጦና ንቦቹ አዲሱ አሰልጣኛቸው ያሬድ ገመቹ ሆኗል።

የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በደረጃ ሰንጠረዡ 12ኛ ላይ በ37 ነጥቦች በመቀመጥ ያጠናቀቁት ወላይታ ድቻዎችን ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር እንደማይቀጥሉ ከተረጋገጠ በኋላ ከቀናት በፊት የሊጉ ጨዋታዎች መጠናቀቂያ ምሽት አንስቶ ሲደራደሩ የነበሩትን አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹን ክለቡ በይፋ በዛሬው ዕለት በሁለት ዓመት ውል መሾሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
ከእግር ኳስ የተጫዋችነት ዓለም ከተገለሉ በኋላ ወደ ስልጠናው ዓለም ጎራ በማለት ከታዳጊ ወጣቶች ስልጠና አንስቶ በክለብ ደረጃ ደቡብ ፓሊስ ፣ ስልጤ ወራቤ እና ኢኮስኮን በከፍተኛ ሊጉ አሰልጣኝነት መምራት የቻሉት አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ በመቀጠል በፕሪምየር ሊግ ደረጃ የሀዋሳ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና በረዳት አሰልጣኝ ያገለገሉ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪምየር ሊጉ ሀድያ ሆሳዕናን በዋና አሰልጣኝነት እየመሩ ውላቸው እስከ ሚጠናቀቅበት ሰኔ 30 ድረስ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ አሰልጣኝ ያሬድ በዛሬው ዕለት አዲሱ የጦና ንቦቹ አለቃ ሆነዋል።
\"\"