ሲዳማ ቡና የመጀመሪያ ፈራሚውን አግኝቷል

በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ የሚመራው ሲዳማ ቡና የግራ መስመር ተከላካዩን የመጀመሪያ የክለቡ ፈራሚ አድርጓል።
\"\"
በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመጨረሻ ሳምንታትን ባስመዘገበው ውጤት በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው እና ከአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ጋር በቀጣዩ ዓመትም የሚቀጥለው ሲዳማ ቡና የመጀመሪያ ፈራሚውን በእጁ ማስገባቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። ደስታ ዮሐንስ ደግሞ የክለቡ አዲሱ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል።
\"\"
እግር ኳስን ከሀዋሳ ታዳጊ ቡድን ከጀመረ በኋላ በመቀጠል በክለቡ ዋናው ቡድንም ጭምር ተጫውቶ ያሳለፈው የግራ መስመር ተከላካዩ ረዘም ያሉ ዓመታትን ካሳለፈበት ሀዋሳ ከተማ ከለቀቀ በኋላ ከ2014 ጀምሮ በአዳማ ከተማ እየተጫወተ ቆይታ አድርጓል። በርከት ካሉ ቡድኖች ጋር ስሙ ሲነሳ የነበረው ተጫዋቹ በመጨረሻም መዳረሻውን በሁለት ዓመት ውል ሲዳማ ቡና መሆኑ ዕርግጥ ሆኗል።