ፈረሠኞቹ እና የጣና ሞገዶቹ የትኞቹን ስታዲየሞች አስመዝግበዋል…?

በአህጉር አቀፍ ውድድሮች የማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቃቸው የሀገራችን ተወካይ ቡድኖች ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ሜዳ ከቀናት በኋላ በይፋ ይታወቃል።

\"\"
የ 2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ባህርዳር ከተማ የአህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማድረግ ቀናት ቀርተዋቸዋል። ሆኖም የእግርኳሱ ቤተሰብ ሀገራችን ባለባት ጥራት ያለው መጫወቻ ሜዳ ዕጥረት ምክንያት የሁለቱም ክለቦች ጨዋታዎች የት ሊደረጉ እንደሚችሉ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት መረጃዎችን ለማጣራት የሞከረችው ድህረገጻችን ሶከር ኢትዮጵያም ጨዋታዎቹ የሚደረግባቸውን ሜዳዎች ካፍ ከፈረንጆቹ August 1 (ሐምሌ 25) በኋላ በይፋ እንደሚያስታውቅ ሰምተናል።

\"\"
በቻምፒዮንስ ሊጉ ከ ኬኤምኬኤም ጋር የተደለደለው ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ስታዲየምን እና የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየምን በቅደም ተከተል ሲያስመዘግብ በአንጻሩ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከ አዛም ጋር የተደለደለው ባህርዳር ከተማ ደግሞ የባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየምን እና የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየምን አንደኛ እና ሁለተኛ አድርጎ ማስመዝገባቸው ታውቋል።