መቻል አሠልጣኝ ሾሟል

ከሰሞኑን ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን የቴክኒክ አማካሪው ለማድረግ ከስምምነት የደረሰው መቻል ዋና አሠልጣኝ ቀጥሯል።
\"\"
ከሁለት ቀናት በፊት የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር የሆኑት አብርሃም መብራቱን በዋና አሠልጣኝነት አልያም በቴክኒክ አማካሪነት ለመሾም ሲደራደር የነበረው መቻል ከደቂቃዎች በፊት ዋና አሠልጣኝ ማግኘቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

\"\"

ክለቡን ለአንድ ዓመት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ያኖሩት አሠልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ናቸው። ዲላ ከተማን በመቀላቀል የስልጠናውን ዓለም የተቀላቀሉት ገብረክርስቶስ ቢራራ በደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የእድሜ ቡድኖችን ያሰለጠኑ ሲሆን ደቡብ ፖሊስን እንዲሁም ወላይታ ድቻን ማሰልጠናቸውም አይዘነጋም። የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ደግሞ በወልቂጤ ከተማ ካሳለፉ በኋላ አሁን በመቻል በፕሪምየር ሊጉ ለማሰልጠን ፊርማቸውን አኑረዋል።
\"\"
አሠልጣኙን የለየው ክለቡም ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የክለቡ የቴክኒክ አማካሪ እንደሚሆኑ ዝግጅት ክፍላችን አረጋግጣለች።