የምስራቁ ክለብ ድሬዳዋ ከተማ ስድስተኛ ፈራሚው የመስመር ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ሆኗል።
ዘግየት ብሎም ቢሆን ወደ ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከገባ በኋላ ተመስገን ደረሰ ፣ ሀምዲ ቶፊቅ ፣ ኤፍሬም አሻሞ ፣ ሔኖክ አንጃ እና ቴዎድሮስ ሀሙን በይፋ ወደ ክለቡ የቀላቀለው ድሬዳዋ ከተማ ስድስተኛው ፈራሚ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዳግማዊ አባይን አስፈርሟል።
ከሺንሺቾ ከተማ ከተገኘ በኋላ በደደቢት ፣ በኢኮስኮ ፣ ወልድያ ከተማ ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ እና የተጠናቀቀውን ዓመት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማሳለፍ ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን ቀጣዩ መድረሻው ድሬዳዋ ሆኗል።