አዲሱ የመቻል ፈራሚ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶበታል

ከወራት በፊት መቻል የተቀላቀለው ዩጋንዳዊ ግብ ጠባቂ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ደረሰው።

ከወራት በፊት መቻልን ለመቀላቀል ፌርማውን አኑሮ ከቡድኑ ጋር ልምምድ የጀመረው ዩጋንዳዊው ግብ ጠባቂ አሊዮንዚ ናፍያን ሀገሩ እንዲወክል ጥሪ ደርሶታል። አሰልጣኝ ሰርጅዮቩች ሚሎቲን ሚቾ በቀጣይ ሳምንት ከኒጀር ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ስብስባቸው ይፋ ስያደርጉ፤ ጥሪ ከደረሳቸው ተጫዋቾች ውስጥም የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ ኢስማኢል ዋቴንጋ ይገኝበታል።

በ2022 ከኡዝቤኪስታን ጋር በነበረው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሀገሩን ማልያ መልበስ የጀመረው ይህ ተጫዋች ለሀገሩ ስድስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል።