ሉሲዎቹ ጥሪ ተደርጎላቸዋል

የብሩንዲ አቻውን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ታውቀዋል።

በ2024 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣርያ መስከረም 9 እና መስከረም 15 የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከብሩንዲ ጋር እንደሚጫወት ይጠበቃል። የሉሲዎቹ ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለጨዋታዎቹ ዝግጅት ለማድረግ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ተጫዋቾቹ ነገ ከ10:00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል በመገኘት ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩም ጥሪ ተላልፏል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር ፦

ግብ ጠባቂዎች

ታሪኳ በርገና (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ቤተልሔም ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)
አበባ አጂቦ (ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ)

ተከላካዮች

ብርቄ አማረ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ብዙአየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ናርዶስ ጌትነት (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ንጋት ጌታቸው (ልደታ ክፍለ ከተማ)
ቤተልሔም በቀለ (መቻል)
ነፃነት ፀጋዬ (መቻል)
ቅድስት ዘለቀ (ሀዋሳ ከተማ)
መንደሪን ክንድይሁን (ሀዋሳ ከተማ)
ፀሐይነሽ ጁላ (ሀዋሳ ከተማ)

አማካዮች

ፂዮን ፈየራ (አዳማ ከተማ)
ኒቦኝ የን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
መሳይ ተመስገን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
አረጋሽ ካልሣ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
መሀድን ሣሀሉ (ሀዋሳ ከተማ)

አጥቂዎች

ሎዛ አበራ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ሴናፍ ዋቁማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ረድኤት አስረሳኸኝ (ሀዋሳ ከተማ)
ቱሪስት ለማ (ሀዋሳ ከተማ)
ንግስት በቀለ (መቻል)
አርያት አዶንግ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ማህሌት ምትኩ (ሲዳማ ቡና)
እሙሽ ዳንኤል (ሀዋሳ ከተማ)
አለሚቱ ድሪቦ (ልደታ ክፍለ ከተማ)