የአሰልጣኝ ራውዳ ዓሊው የቅዱስ ጊዮርጊስ ዕንስት ቡድን ወደ 18 የሚጠጉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ያለፉትን ዓመታት እየተወዳደረ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለ2016 የውድድር ዘመንም በአሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ መሪነት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር ከግማሽ በላይ ስብስቡን በአዳዲስ ተጫዋቾች አዋቅሯል። በዚህም መሠረት ወደ አስራ ስምንት የሚጠጉ አዳዲስ ተጫዋቾችን ቡድኑ አስፈርሟል።
ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂዎች ሠርካለም ዓባይነህ ከአቃቂ ፣ ቤዛዊት ቶራ ከኦሮሚያ ሊግ ፣ ለምለም ተሻገር ከለሚ ኩራ ፣ ተከላካዮች ቤዛዊት ተስፋዬ ከኢትዮጵያ ቡና ፣ ሳምራዊት በጋሻው ከጉለሌ ፣ ቃልኪዳን ዓለማየሁ ከስፖርት አካዳሚ ፣ መቅደስ ታፈሰ ከንፋስ ስልክ ፣ ሠርካለም ሻፊ ከጉለሌ ፣ አማካዮች ሜሮን አበበ ከልደታ ፣ ተስፋነሽ አዳነ ከቂርቆስ ፣ ሀና ታደሰ ከሱሉልታ ፣ በአምላክ ተፈሪ ከስፖርት አካዳሚ ፣ አጥቂዎች ሰላማዊት ኃይለስላሴ ከአርባምንጭ ፣ ዓለም ባይቻ ከንፋስ ስልክ ፣ ምህረት ቶንጆ ከአዲስ አበባ ፣ አልማዝ ግርማይ ከስፖርት አካዳሚ ፣ ሐርሜላ ይገዙ ከንፋስ ስልክ እና ምስራቅ ዛቶ ከጉለሌ ናቸው።