ኢትዮጵያዊው አጥቂ ዑመድ ኡኩሪ ሌላኛውን የኦማን ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለብ በይፋ ተቀላቅሏል።
በ2007 ወደ ግብፅ ሊግ አምርቶ አል-ኢትሀድ አሌክሳንድሪያን ፣ ኤ ኤን ፒ ፒ አይ ፣ አል-ኤንታግ ኤል-አረቢ ፣ ሶሞሀ እና አስዋን ሲጫወት የቆየው እና በ2014 የውድድር ዘመን ለሀዲያ ሆሳዕና ተጫውቶ
ባሳለፍነው ዓመት ወደ ኤዥያዊቷ ሀገር ኦማን ያቀናው ዑመድ በሀገሪቷ ቆይታው ለሁለተኛ ክለብ ፈርሟል።
እስካሁን አል-ሱዋይክ በተባለ ክለብ በመጫወት የኦማን ቆይታ የነበረው አጥቂው አሁን ደግሞ ወደ ሌላኛው የኦማን ፕሪምየር ሊግ ክለብ ተሳታፊ የሆነው ናፍት አል ዋሳት የተባለን ክለብ በይፋ ስለ መቀላቀሉ ሶከር ኢትዮጵያ ለማወቅ ችላለች። ከተመሠረተ 15 ዓመታቾችን ብቻ ያስቆጠረው ናፍት አል ዋሳት በዘንድሮው የኦማን ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው ከ20 የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ካደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በአንድ ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።