ካስትል ዋንጫ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ለ9ኛ ጊዜ የተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ካስትል ዋንጫ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ስፖንሰር ያደረገው ውድድር ዘንድሮ በበርካታ ተመልካቾች የደመቀ ሲሆን በርካታ ወጣት ተጫዋቾችም ታይተውበታል፡፡

በፍፃሜው የተገኛኙት ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መደበኛውን ዘጠና ደቂቃ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡ በጨዋታው ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት ባንኮች ሲሆኑ ከቀኝ መስመር ፊሊፕ ዳውዚ ያጠፈውን ኳስ አዲስ ፈራሚው አብዱልከሪም ሃሰን ከመረብ አሳርፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና የአቻነት ግብ የተቆጠረችው ደግሞ በ79ኛው ደቂቃ በቢንያም አሰፋ አማካኝነት ነው፡፡

አሸናፊውን ለመለየት ከተሰጡት አምስት የመለያ ምቶች ባንክ ሁሉንም ሲያስቆጥር ከኢትዮጵያ ቡና በኩል ጋቶች ፓኖም አምክኖ ኢትዮጵያ ንገድ ባንክ 6-5 በሆነ አጠቃላይ ውጤት የ2007 ዓ.ም የአዲስ አበባ ካስትል ዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡

ከፍፃሜው በፊት በተደረገው የደረጃ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መከላከያን 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ሶስተኛ ደረጃን አግኝቶ አጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ ካስትል ዋንጫ አበይት ሽልማቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

የዋንጫ ባለቤት – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ኮከብ ተጫዋች – አብዱልከሪም ሃሰን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

ኮከብ ግብ አግቢ – ቢንያም አሰፋ (ኢትዮጵያ ቡና/5 ግብ)

ኮከብ አሰልጣኝ – ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም (ኢትዮጵያ ንገድ ባንክ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *