“ያሰብነውን ነገር ማሳካት አልቻልንም” አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
“በጣም ጠንካራ ቡድን ነው ያለን” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ
በሣምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ፈረሠኞቹ በአማኑኤል ኤርቦ ብቸኛ ግብ ዐፄዎቹን ከረቱ በኋላ አሰልጣኞቹ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ
ስለ ጨዋታው…
“ጨዋታው ጠንካራ ጨዋታ ነው። ይሄን መገመት ከባድ አይደለም። በእነሱ በኩልም ጥሩ ጥረቶች ነበሩ ባላንስ የሆነ ጨዋታ ነው በሁለታችንም ክፍት የሆነ ጨዋታ ነው የነበረው። የግብ ዕድሎችን በመፍጠር ኳስ በመቆጣጠር በሁለቱም በኩል ጥሩ ነበር። ፋይናሊ ግን ያሰብነውን ነገር ማሳካት አልቻልንም።”
የዓለምብርሃን ቀይ ካርድ ስለፈጠረው ተጽዕኖ አለ…
“አዎ! ክሊር ነው እንደዚህ ዓይነት ትልቅ ጨዋታ ላይ በሰው ቁጥር የምታንስ ከሆነ ክፍተት መፈጠሩ አይቀርም። በቡድናችን በርካታ ልጆች በጉዳት የሉም። እነዛን ጠጋግነህ እየተጫወትክ እንደገና ደግሞ አንድ ሰው ሲጎድልብህ ያስቸግራል። ያም ቢሆን ግን በኋላም ዕድሎችን ለመፍጠር ሞክረን ነበር። በተለይም ጎዶሎ ከሆንን በኋላ ጌሙን ተቆጣጥረን በመልሶ ማጥቃት የጎል ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረት አድርገናል።”
የቡድኑ ጠንካራ እና ደካማ ጎን…
“የመጫወት ፍላጎታችን ፤ ተጭነን ለመጫወት ሙከራችን ሁሉም ነገር ጥሩ ነበር። እንደዚህ ዓይነት ጨዋታዎች ላይ ከትልቅ ቡድን ጋር በዚህ ደረጃ መጫወት በራሱ ትልቅ ነገር ነው። ኦፍ ኮርስ የጎል ዕድሎችን ከዚህ በበለጠ መፍጠር ይኖርብናል። የሚገኙ አጋጣሚዎችን ወደ ግብ የመቀየር ነገር ላይም ክፍተቶች ይታያሉ። ብዙ ጎል ካገቡ አራት አምሥት ክለቦች አንዱ ነን ግን ያሉትን ወደ ግብ መቀየር መቻል ነው የሚጎድለን።”
አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ስለ ጨዋታው…
“በጣም ጥሩ ነበር። ፈርስት ሃፍ ሙሉ በሙሉ ዶሚኔት አድርገናቸዋል። ሰከንድ ሃፍም የተሻለ ነገር ሠርተናል። በተሻለ ወደ ጎል እንገባ ነበር ጎልም አስቆጥረናል ፤ ጥሩ ጨዋታ ነበር። ከሽንፈት እና ከአቻ ነበር የመጣነው ልጆቼ የሠራነውን እና ማድረግ ያለባቸውን በጣም ጥሩ ነገር አድርገው ውጤቱን ይዘን ወጥተናል። ከዚህም በላይ ጎሎች መግባት ነበረባቸው። የተሻለ ጥሩ ነገር ማድረግ የሚችሉ ልጆች አሉ ያንን አድርገው አሸንፈን ወጥተናል።”
ስለቡድኑ ጠንካራ እና ደካማ ጎን…?
“ምንም ክፍተት አላየሁም። በጣም ጠንካራ ቡድን ነው ያለን ፤ ሕብረታችን። የተሰጣቸውን ታክቲክ በአግባቡ እየተገበሩ መሥራት ያለባቸውን በየዞኑ ከዲፌንሲቭ እስከ አታኪንግ ሲቹዌሽን ማድረግ ያለባቸውን አድርገው ብዙ ኳሶችን ሞክረናል። አሁንም ከዚህ በላይ ማድረግ ይችላሉ። በጣም ጥሩ ነገር ነው የሠሩት ፤ ውጤቱም ይመሰክራል።”
የዛሬው ውጤት ለቀጣይ ምን መነሳሳት ስለመፍጠሩ…
“ትልቅ ጉልበት ነው። ልጆቹን እያየሃቸው ነው ስፕሪታቸው ማድረግ የሚፈልጉትን ከዚህም በላይ ማድረግ ይችላሉ። አቅማቸው ትልቅ ነው። የጣልናቸውም ውጤቶች ብዙ ከተቃራኒ ቡድን ገጽታ እና አንዳንድ ነገሮች ከራሳችን ቲም ኮንሰንትሬሽን ማጣት ነው። ኮንሰንትሬትድ ሆነን ማድረግ የምንችለውን ነገር ከሠራን እንዴት ውጤት እንደምናመጣ እና የጎል ዕድሎችን እንደምንሞክር ዛሬ ታይቷል ጠንካራ ጨዋታ ነው በሁለታችንም በኩል።”
ወደ መጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የተጋጣሚ ቡድን ጫና…
“ትክክል ነው። የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ ሁሉም ነው ነቅለው የወጡት። በቅጣት ምት በአንዳንድ ሎንግ ፓሶች ነበር የሚጫወቱት ይሄ ጥንቃቄ እና ኦርጋናይዜሽን ይፈልጋል። እየመራህ ነው ዝም ብለህ በርህን ከፍተህ አትሄድም። ብዙ ደቂቃዎች አይደሉም አሥር ደቂቃዎች አይሞሉም። ግን ጥሩ ነገር አድርገው ኦፌንሲቭም ዲፈሰንሲቭም ልጆቼ በጥሩ ነገር ጥሩ ውጤት ይዘው ወጥተዋል።”