የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ2016 የኮከብ ተጫዋቾች እጩዎችን በየዘርፉ ይፋ አድርጓል።
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማሮውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አድርጎ ወደ ድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በማቅናት የመጨረሻ ምዕራፉን ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እያከናወነ ሊገባደድ የሁለት ሳምንታት ዕድሜ ቀርቶታል።
ሆኖም ዛሬ ፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር የውድድር ዓመቱን ኮከብ ተጨዋቾች በሚከተሉት ዘርፎች ይፋ አድርጓል።
የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች
1. ባሲሩ ኦማር (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
2. ሽመልስ በቀለ (መቻል)
3. ፈቱዲን ጀማል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
4. ቸርነት ጉግሳ (ባህር ዳር ከተማ)
5. ዓሊ ሱሌይማን (ሀዋሳ ከተማ)
6. ከነዓን ማርክነህ (መቻል)
የውድድር ዓመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ እጩዎች
1. አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ መድን)
2. ሰዒድ ሀብታሙ (አዳማ ከተማ)
3. ፍሬው ጌታሁን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
የውድድር ዓመቱ ወጣት ተስፈኛ ተጫዋች እጩዎች
1. ወገኔ ገዛኸኝ (ኢትዮጵያ መድን)
2. ተመስገን ብርሃኑ (ሀዲያ ሆሳዕና)
3. ዮሐንስ መንግሥቱ (መቻል)
4. በፍቃዱ ዓለማየሁ (ኢትዮጵያ ቡና)
5. መድን ተክሉ (ወልቂጤ ከተማ)
6. ቢኒያም አይተን (አዳማ ከተማ)
* ተመልካቾች እስከ ሰኔ 28/2016 ድረስ በአክሲዮን ማኅበሩ የቴሌግራም ቻናል በመግባት ድምፅ መስጠት እንደሚችሉም ተነግሯል።