ሲዳማ ቡና የመስመር አጥቂ አስፈርሟል

ከደቂቃዎች በፊት የአንድ ተጫዋችን ዝውውር ያጠናቀቀው ሲዳማ ቡና ተጨማሪ አንድ ተጫዋች ማስፈረሙ ታውቋል።

በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የሚመሩት ሲዳማ ቡናዎች ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት ከደቂቃዎች በፊት አበባየሁ ሀጂሶን ማስፈረማቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት በመቻል እግር ኳስ ክለብ ቆይታ የነበረው የመስመር ተጫዋቹ ሳሙኤል ሳሊሶን ማስፈረማቸው እርግጥ ሆኗል።

በ2007 ሼር ኢትዮጵያን ለቆ ወደ መቻል ካመራ በኋላ በቡድኑ አራት የውድድር ዓመታት ያሳለፈው ሳሙኤል የሊጉን ዋንጫ ባነሳበት መቐለ 70 እንደርታ ጨምሮ በወልቂጤ ከተማና ሰበታ ከተማ ሲጫወት ከቆየ በኋላ የመጀመርያ የፕሪምየር ጨዋታውን ወደ አደረገበት መቻል ዳግም ተመልሶ ሁለት የውድድር ዓመታት መቆየቱ ሲታወስ አሁን ደግሞ በሁለት ዓመት ውል ወደ ሲዳማ ቡና አቅንቷል።