“ህጉ ማስከበር ካልቻልኩኝ እኔም ጓደኞቻችን በጊዜ ወደ ቤታችን እንሄዳለን። ምን አንሰራም”መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ውዝግቦች እያስነሳ የሚገኘው የዘንድሮው ተጫዋቾች ዝውውር የተለያዩ ሀሳቦች እየተነሱበት ይገኛል።


ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የካፒታል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ የሊግ ካምፓኒው የቦርድ ሰብሳቢ ከመድረኩ ጠንከር ያለ አቋማቸውን እያንፀባረቁበት እንደነበር ከስር ከስር ዘገባዎችን ማቅረባችን ይታወቃል። የሚዲያ አካለትም የተለያዩ ጥያቄዎችን እያነሱ ሲሆን “የወጣውን አዲስ መመርያ ለመፈፀም ጉልበቱ አላቹሁ ወይ ?” ተብለው የተጠየቁት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ተከታዩን ሀሳብ ገልፀዋል።

“ ህጉን ለማስፈፀም ጉለበት አላቹሁ ወይ ላለቹሁን ? አዎ ጉልበት አለን ብለን እናምናለን። ለምን ብትሉ በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ሌብነት ተፈፅሟል ሌብነቱን አስቀሩለት የሚል አካል ቢመጣ እኔ ላይ ምን ሊደርስ እንደሚችል አላቅም። እኔ ደግሞ ብልፅግና ይሁን ፣ ሀብታምም ይሁን ወላ የፈለጋቹሁትን ስም ስጡት ህጉ ከተጣሰ ይሄን ህግ ለማስከበር ካልቻልኩኝ እኔም ጓደኞቻችን በጊዜ ወደ ቤታችን እንሄዳለን። እርግጠኛ ነኝ ምንም የምናገኘው ጥቅም የሚቀርብን የለም። ለዚህ ብለን ክብራችንን፣ እምነታችን ዋጋ አንከፍልም። እኔ እድሜልኬን አላደረኩም። አሁንም አላደርግም። ስለዚህ ሙሉ ጉልበቱ አለን። እርግጠኛ ነኝ መንግስትም ይደግፈናል።”