የጦና ንቦቹ ረዳት አሰልጣኝ ታናሽ ወንድም የሆነው ተጫዋች ቡድኑን ተቀላቅሏል።
በክረምቱ የፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ላይ የነቃ ተሳትፎን በማድረግ ላይ የሚገኘው የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹው ወላይታ ድቻ እስከ አሁን አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊጉ እና ከፕሪምየር ሊጉ ክለቦች ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ የወላይታ ድቻ የቀድሞው አምበል እና የአሁኑ ደግሞ ረዳት አሰልጣኝ በመሆኑ ከቡድኑ የሚገኘው ግዛቸው ጌታቸው ታናሽ ወንድም የሆነው ሠለሞን ጌታቸው ክለቡን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል።
በመስመር አጥቂነት በከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ በነበሩት ሶዶ ከተማ ፣ ሀምበሪቾ ፣ ጋሞ ጨንቻ ፣ ወልድያ እና ያለፉትን ዓመታት ደግሞ በነቀምት ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ወደ ትውልድ ሀገሩ ክለቡ ተመልሷል።