መቐለ 70 እንደርታ ወደ ዝውውሩ ገብቷል

ምዓም አናብስት ጋናዊውን ተከላካይ ለማስፈረም ተስማምተዋል።


ቀደም ብለው አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐየን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት መቐለ 70 እንደርታዎች የክረምቱ የመጀመሪያ ዝውውራቸውን ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል። በዛሬው ዕለት ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው ደግሞ ጋናዊው ተከላካይ ሸሪፍ መሐመድ ነው።

ባለፈው የውድድር ዓመት ከአሻንቲ ኮቶኮ ጋር ያሳለፈው ይህ የሃያ ሁለት ዓመት ተከላካይ ከቡድኑ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ በአንድ ዓመት ውል የኢትዮጵያውን ክለብ ለመቀላቀል ተስማምቷል። ከዚህ ቀደም በፈረንሣይ ውስጥ የጥቂት ጊዜ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በክለብ ደረጃ እግር ኳስ በጀመረበት ስታደፋስት እና አሻንቲ ኮቶኮ መጫወት የቻለ ሲሆን አልጄርያ ባዘጋጀችው የ2022 የቻን ዋንጫ ላይ እስከ ሩብ ፍጻሜው በተጓዘ የጋና ብሔራዊ ቡድን ውስጥም አባል ነበር።