ኬንያ ፖሊስ ተሸነፈ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ የቡና ተጋጣሚን አሸነፉ።


ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ ያቀናው ኢትዮጵያ ቡናን የሚገጥመው ኬንያ ፖሊስ በአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሽንፈት አስተናገደ። ላለፉት አስር ቀናት በኬንያ ዝግጅት ስያደርግ ቆይቶ ወደ ዩጋንዳ በማቅናት ከቫይፐርስ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ያካሄደው ቡድኑ የሁለት ለባዶ ሽንፈት ደርሶበታል። በቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪች የሚመሩት ቫይፐርሶች ኬኔት ኪሜራ እና በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይሮ የገባው ጉስቶ ሙሎንጎ በጭማሪ ሰዓት ባስቆጠሯቸው ግቦች ጨዋታውን አሸንፈዋል፤ በኬንያ ፖሊስ በኩልም ከዚህ ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስ የምናውቀው ፓትሪክ ማታሲ ተሰልፎ ሲጫወት ከኢትዮጵያ ቡና በውዝግብ የተለያዩት አሰልጣኙም የዩጋንዳው ስራቸው በድል ጀምረዋል።

ቡድናቸውን ለማጠናቀር ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙት ኬንያ ፖሊሶች እስካሁን ድረስ ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾች ስያስፈርሙ ከሶስት ተጫዋቾች ጋር ተለያይተዋል።