ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ አስፈርሟል

ከክልል ክለቦች ሻምፒዮና ቡናማዎቹ ወጣቱን አጥቂ የግላቸው አድርገዋል።

ኢትዮጵያን በመወከል በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚካፈለው ኢትዮጵያ ቡና ከአህጉራዊ ውድድሩ በተጨማሪ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን ባጣቸው በርካታ ተጫዋቾች ምትክ እስከ አሁን ከከፍተኛ ሊጉ እና ከሀገር ውጪ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ አጥቂው ሀብታሙ አሸናፊን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ ዲቪዚዮን ተሳታፊ በነበረው እና የከተማውን ዋንጫ በማንሳቱ በክልል ክለቦች ዋንጫ ላይ ተካፋይ በነበረው ፉሪ ክፍለ ከተማ ውስጥ ድንቅ እንቅስቃሴ ያደረገው ሀብታሙ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን በአራት ዓመታት ውል መድረሻው ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።