አዞዎቹ የተጨማሪ ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል

የተጫዋቾችን ውል በማራዘም የተጠመደው አርባምንጭ ከተማ የሦስት ተጫዋቾችን ውል አድሷል።

በአሰልጣኝ በረከት ደሙ መሪነት በቀጣዩ የውድድር ዘመን በፕሪምየር ሊጉ ተካፋይ የሚሆነው አርባምንጭ ከተማ ከሰሞኑ በክለቡ የነበሩ የበርካታ ተጫዋቾችን ኮንትራት እያራዘመ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ አመት ውላቸውን አድሶላቸዋል።

ከጋሞ ጨንቻ የተገኘው እና ያለፉትን አራት ዓመታት በክለቡ የነበረው የመስመር አጥቂው አሸናፊ ተገኝ ፣ ከታችኛው ቡድን የተገኘው ግብ ጠባቂው ሰራዊት ሰያ እና የመስመር አጥቂው አላዛር መምህሩን ውል ያደሰ ሲሆን አመሻሹን ደግሞ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾች ለማስፈረም የፌዴሬሽን ተወካይን በክለቡ መቀመጫ በመጥራት የሚያፀድቅም ይሆናል።