የተከላካይ አማካዩ ማረፊያው ታውቋል

አርባምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ተጫዋቹን በእጁ አስገብቷል።

ለ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ተጠናክረው ለመቅረብ ይረዳቸው ዘንድ ቀደም በማለት በክለባቸው ውስጥ ውላቸው ተጠናቆ የነበሩ ነባር ተጫዋቾችን ውል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በማራዘም ተጠምደው ያሳለፉትን አርባምንጭ ከተማዎች አሁን ደግሞ የመጀመሪያ የሆነውን የአዲስ ተጫዋች ዝውውር ያጠናቀቁ ሲሆን የተከላካይ አማካዩ ይሁን እንዳሻው ደግሞ የክለቡ አዲሱ ፈራሚ መሆኑን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ይፋ አድርጓል።

እግር ኳስን ከትውልድ አካባቢው መተሐራ የጀመረው እና በመቀጠል በድሬዳዋ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ላለፉት አራት ዓመታት ደግሞ በፋሲል ከነማ ቤት ቆይታን ማድረግ የቻለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ አማካዩ ተጫዋቹ በቀጣዩ የውድድር ዓመት አዲሱ ክለቡ አዞዎቹ መሆናቸው በዛሬው ዕለት ተረጋግጧል።