ንግድ ባንክ የወሳኙን አጥቂ ውል አራዝሟል

የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቡድኑን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ውል አድሷል።


ካሳለፉት የዘንድሮ የውድድር ዘመን አንፃር የተቀዛቀዘ ዝውውር እየፈፀሙ የሚገኙት የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የአብዱልከሪም መሐመድን እና ቢንያም ካሳሁንን በስብስባቸው የቀላቀሏቸው ብቸኛ ተጫዋቾች ናቸው።

በተጨማሪ የቡድኑን የኋላ ደጀን የጋናዊውን ካሌብ አማንኩዋ ውል ያራዘመው ክለቡ አሁን ደግሞ ከብዙ ድርድር በኋላ ወሳኝ አጥቂውን አዲስ ግደይን ለተጨማሪ ዓመት ዓመታት በቡድኑ የሚቆይበትን ውል ማራዘሙ ታውቋል።

ለተከታታይ ሦስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ከፈረሰኞቹ እና ከንግድ ባንክ ጋር ያነሳው አዲስ ከፈታኝ የጉልበት ጉዳት በኋላ በዘንድሮ ዓመት አስደናቂ አቋሙን ያስመለከተን ሲሆን አስራ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ማጠናቀቁ ይታወሳል።