ሲዳማ ቡና ተስፈኛውን አጥቂ አስፈርሟል

ከፍተኛ ዝውውር እየፈፀመ ያለው ሲዳማ ቡና ወጣቱን የመስመር አጥቂ አስፈርሟል።

ለከርሞ ጥሩ ተፎካካሪ ቡድን ለመገንባት ከፍተኛ ዝውውር እየፈፀሙ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የመስፍን ታፈሰን፣ ሳሙኤል ሳሊሶ፣ አበባየሁ ሀጂሶ፣ ሀብታሙ ታደሰ፣ ሬድዋን ናስር፣ ፍራኦል መንግስቱ እና የያሬድ ባዬን ዝውውር በማጠናቀቅ የደስታ ደሙን እና ማይክል ኪፕሩቪ ውል ማራዘማቸው ይታወቃል።

አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ከፍተኛ ሊግ በማዞር የወጣቱን የመስመር አጥቂን ኤርሚያስ ደጀኔን ማስፈረማቸው ታውቋል። የእግርኳስ ህይወቱን በይርጋለም የጀመረው ኤርሚያስ በደቡብ ፖሊስ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት በንብ ክለብ በመስመር አጥቂ ጥሩ የውድድር አመት ማሳለፉ ሲታወቅ ለሲዳማ ቡናም ለሁለት ተከታታይ ዓመት የሚቆይበትን ፊርማውን ማኖሩ ታውቋል።