ቢኒያም በላይ ማረፊያው ታውቋል

ሀዋሳ ከተማ የወሳኝ ተጫዋች ዝውውር ለመፈፀም ተስማምቷል።

በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመራው ሀዋሳ ከተማ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ራሱን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ በመግባት የመጀመሪያ ፈራሚውን በእጁ ሲያስገባ የመስመር እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ቢኒያም በላይ ደግሞ የመጀመሪያው የክለቡ ፈራሚ መሆኑንን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በ2009 መጨረሻ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ወደ ጀርመን አምርቶ የሙከራ ጊዜ ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን ወደ አልባንያው ክለብ ስከንደርቡ አምርቶም ከክለቡ ጋር የሊግ ዋንጫን ማንሳቱ አይዘነጋም። በመቀጠል ወደ ስዊድን በማቅናት ለስሪያንስካ እና ኡሚያ ክለቦች የተጫወተ ሲሆን ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ለሲዳማ ቡና ተጫውቶ በመቀጠል ደግሞ በመቻል እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ጥሩ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ ቀጣይ መዳረሻው ሀዋሳ ከተማ ሆኗል።