ሲዳማ ቡናዎች ተጨማሪ ተጫዋች በእጃቸው አስገብተዋል

እስከ አሁን ስድሰት ተጫዋቾች አስፈርመው የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች ስድስተኛ ፈራሚያቸው አጥቂው ሀብታሙ ታደሠ ለመሆን ተቃርቧል።

ለ2017 የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት አበባየሁ ሀጂሶ ፣ ሳሙኤል ሳሊስ ፣ ፍራኦል መንግሥቱ ፣ መስፍን ታፈሰ፣ ያሬድ ባዬ እና ሬድዋን ናስርን በይፋ ያስፈረሙት ሲዳማ ቡናዎች ሰባተኛ ፈራሚያቸው አጥቂው ሀብታሙ ታደሠ ሆኗል።

ከቡሌ ሆራ ከተገኘ በኋላ በወልቂጤ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ከባህርዳር ከተማ ጋር ያሳለፈው አጥቂው ሀብታሙ ታደሠ ወደ ወላይታ ድቻ ለማምራት ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ሳይስማማ በመቅረቱ መዳረሻው ሲዳማ ቡና ሆኗል።