አርባምንጭ ከተማ የግራ መስመር ተከላካይ አስፈረመ

ወጣቱ የግራ መሰመር ተከላካይ ካሌብ በየነ የአዞዎቹ ሦሰተኛው ፈራሚ ሆኗል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀጣይ የውድድር ዘመን ተካፋይ የሆኑ አርባምንጭ ከተማዎች የአሰልጣኝ በረከት ደሙ ውል በማደስ በክለቡ የነበሩ ወደ ዘጠኝ የሚጠጉ ነባሮችን ኮንትራትም ለተጨማሪ ዓመታት የማራዘም ስራን ከሰሩ በኋላ በትላንትናው ዕለት ወደ ውድድር በመግባት ይሁን እንዳሻው እና ሙሉጌታ ካሳሁን ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሦስተኛው አዲስ ተጫዋች ካሌብ በየነ ሆኗል።

ከሀድያ ሆሳዕና ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ላለፉት አራት ዓመታት በግራ መስመር ተከላካይነት በክለቡ ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች ውሉ መቋጨቱን ተከትሎ አሳዳጊ ክለቡን በመተው ቀጣይ መዳረሻው አዞዎቹ ቤት ሆኗል።