ቦና ዓሊ ወደ ምዓም አናብስት ለመቀላቀል ተስማምቷል

መቐለ 70 እንደርታዎች የፊት መስመር ተጫዋቹን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ቀደም ብለው አራት ተጫዋቾች ለማስፈረም የተስማሙት መቐለ 70 እንደርታዎች አሁን ደግሞ በመስመርና በፊት አጥቂነት መጫወት የሚችለውን ቦና ዐሊን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
ፎረስት በሚባል ሻሸመኔ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የጃማይካዎች ቡድንና በአምቦ አካዳሚ እግርኳስን የጀመረው ወጣቱ ተጫዋች በክለብ ደረጃ ለሻሸመኔ ታዳጊና ዋናው ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን በመቀጥልም በፕሪሚየር ሊጉ ለጅማ አባ ጅፋር ካለፉት ዓመታት ጀምሮ ደግሞ በአዳማ ከተማ መጫወት ችሏል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ሀያ አምስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 1495 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ተጫዋቹ በውድድር ዓመቱ አምስት ግቦች ማስቆጠር ሲችል ከአዳማ ከተማ ወሳኝ ተጫዋቾች አንዱ ነበር።