ሀድያ ሆሳዕና ሁለተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል

በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ የሚመራው ሀድያ ሆሳዕና የመስመር አጥቂውን ሲያስፈርም የአማካዩን ውል አድሷል።

ከአሰልጣኙ ግርማ ታደሠ ውል ማራዘም በኋላ የቃለአብ ውብሸት ፣ ከድር ኩሊባሊ እና ሳሙኤል ዮሐንሰን ውል ያራዘሙት እና እዮብ አለማየሁን አዲሱ ፈራሚ ያደረጉት ሀድያ ሆሳዕናዎች በዛሬው ዕለት ሁለተኛ ተጫዋቻቸውን ዝውውር ሲፈፅሙ የአማካያቸውን ኮንትራት ደግሞ አራዝመዋል።

ክለቡን የተቀላቀለው አዲሱ ተጫዋች የመስመር አጥቂው በረከት ወንድሙ ነው። ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን የተገኘው እና በዋናው ቡድንም መጫወት የቻለው ተጫዋቹ በሀምበሪቾ የከፍተኛ ሊግ እና በተጠናቀቀው ዓመት የፕሪምየር ሊግ ቆይታን ከተሰናባቹ ክለብ ጋር ካደረገ በኋላ ለአንድ ዓመት የሀድያ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል።

ቡድኑ ከበረከት በተጨማሪ በሀድያ ሌሞ እና ቡራዩ ከተማ እንዲሁም ላለፉት ሁለት ዓመታት በክለቡ የነበረውን የመለሠ ሚሻሞን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።