ወላይታ ድቻ ስድስተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል

የጦና ንቦቹ የቀድሞው አጥቂያቸውን በድጋሚ መልሰዋል።

በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ መሪነት በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሙሉቀን አዲሱ ፣ ቴዎድሮስ ታፈሠ ፣ ውብሸት ክፍሌ ፣ መሳይ ሠለሞን እና ምንተስኖት ተስፋዬን በእጃቸው ያስገቡት ወላይታ ድቻዎች ስድስተኛው የክለቡ ፈራሚያቸው የቀድሞው አጥቂያቸው ያሬድ ዳርዛ ሆኗል።

ከሶዶ ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው እና በቀድሞው ኢትዮጵያ ውሀ ስራ ፣ አርባምንጭ ከተማ እና ከ2013 ጀምሮ ደግሞ ከከፍተኛ ሊግ እስከ ፕሪምየር ሊጉ ድረስ ለአራት ተከታታይ ዓመታት በኢትዮጵያ መድን ያሳለፈው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ያሬድ ዳርዛ በሁለት ዓመት ውል ከዚህ ቀደም ተጫውቶ ወዳሳለፈበት ወላይታ ድቻ በይፋ ተመልሷል።