ኢትዮ ኤሌክትሪክ አጥቂ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል

በፋሲል ከነማ የእስካሁኑን የእግርኳስ ህይወቱን ያሳለፈው አጥቂ ወደ አዲስ አዳጊዎቹ ሊያመራ ነው።

ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ሊጉ የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ዝውውሩ በመግባት ከዚህ ቀደም ስድስት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ በመቀላቀል የነባሮቹ ውል በማደስ ወደ ዝውውሩ መግባቱ ይታወሳል። ቡድኑ አሁን ደግሞ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ሲያያዝ የቆየውን የፊት መስመር ተጫዋቹ ናትናኤል ገብረጊዮርጊስን የግሉ ለማድረግ ከጫፍ ደርሷል። በውድድር ዓመት በሀያ አንድ ጨዋታዎች ተሳትፎ 905 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው አጥቂው ከአራት ዓመት የፋሲል ቆይታ በኋላ ከአሳዳጊ ክለቡ ተለያይቶ ወደ አዲስ አዳጊው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ እየተመሩ ዳግም በፕሪምየር ሊጉ ለመሳተፍ በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኘው ክለቡ በዛሬው ዕለት ተጨማሪ ተጫዋቾች ለማስፈረም በሂደት ላይ ይገኛል።